ቀጣዩ የኀይል ትኲረት

Avatar By admin Feb 10, 2024

ኢትዮጵያ ከታዳሽ የኀይል አማራጮች (ማለትም ከውሃ፣ ከነፋስ እና ከጸሐይ) ከ60,000 ሜጋ ዋት (Mega Watt) የማመንጨት ዐቅም እንዳላት ይታመናል። ከዚህ ውስጥ ከጸሐይ (Solar) 4.5 kWh/m2 እስከ 7.5 kWh/m2 ኀይል በቀን ማግኘት እንደሚቻል ጥናቶች ይጠቊማሉ። እስካሁን ባለው ሂደት የኢትዮጵያ ትልቊ የኀይል ምንጭ ውሃ እንደሆነ ይታወቃል። ይኸውም ካለው አጠቃላይ የኀይል ምጣኔ 90 እጅ የሚሸፍነው ውሃ ነው። ነገር ግን በውሃ ላይ ብቻ ጥገኛ የሆነ የኀይል አቅርቦት በድርቅና በተልያዩ ተፈጥሮአዊና ሰው ሠራሽ ችግሮም ምክንያት የአገሪቱን የኀይል ፍላጐት ማርካት አዳጋች አድርጐታል። ከዚህ የተነሣ መንግሥት አማራጮችን የማብዛት ዕቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ከአማራጮች መካከል አንዱና ዋንኛው የጸሐይ የኀይል አማራጭ ነው። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ በተለያዩ አየገሪቱ ክፍሎች ብዙ በጸሐይ ኀይል የሚሠሩ ቊሳቊሶች ተተክለዋል። የአርባምንጭ መካነ ኢየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅ ባደረገው ጥናት በጋሞ ዞን ብቻ ከ25 በላይ በሚሆኑ ቦታዎች ላይ የጸሐይ ፓኔሎች (Solar panels) ተተክለው ሥራ እየሠሩ ይገኛሉ። የጸሐይ ኀይል አማራጭ ተጠቃሚ ተቋማትም የጤና፣ የግብርና፣ የትምህርት፣ የኀይል አቅራቢ ድርጅቶች፣ ቴሌኮምዩኒኬሺን ወዘተ. . . ይገኙበታል። ነገር ግን የጸሐይ ኀይል አማራጮቹ በትናንሽ ብልሾቶች ምክንያት አገልግሎት እንደሚያቆሙ ባደረግነው ጥናት አረጋግጠናል። ዘርፉ አዲስ በመሆኑ በሙያ የሠለጠነ የሰው ኀይል እጥረት እንዳለም መገንዘብ ችለናል።

ከዚህ የተነሣ የአርባምንጭ መካነ-ኢየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ-ክርሲያን መካነ-ኢየሱስ ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን (DASSC) እና ከአድቨንቲስት ልማትና ተራድዖ ድርጅት (ADRA) ጋር በመተባበር የአጭር ጊዜ ሥልጠና መስጠት ጀምሯል። ሥልጠናው የሚያካትታቸው ይዘቶች የሚከተሉት ናቸው።

የጸሐይ(solar) ቴክኖሎጂ:-

• ዲዛይን

• ተከላ

• ጥገና እና

• የሥራ ፈጠራ ክህሎት ናቸው

ሥልጠናውን የወሰዱ ሰዎች የሚያገኙት የሥራ ዕድል፦

• የጸሐይ ቴክኖሎጂ ዕቃዎችን ማስመጣት፣ ማከፋፈል ወይም መሸጥ

• የጥገና ባለሙ (ቴክንሺያን) መሆን

• በጸሐይ ኀይል የሚንቀሳቀስ የራስ ሥራዎች ማለትም ጸጒር ቤት፣ መስኖ ሥራ፣ ዲኤስ ቲቪ አገልግሎት፣ ወዘት . . . መፍጠር

• በተለያዩ የመንግሥት መ/ቤቶች ውስጥ ተቀጥሮ መሥራት

የአርባምንጭ መካነ ኢየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅ!

Avatar

By admin

Related Post