ወጣቶች ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ የዕውቀትና የክህሎት ሥልጠና ሊያገኙ እንደሚገባ ተገለጸ

Avatar By Guwad K. Mar 19, 2024

ወጣቶች ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ የዕውቀትና የክህሎት ሥልጠና ሊያገኙ እንደሚገባ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ መጋቢት 10/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ወጣቶች ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ የሶላር ቴክኖሎጂ ላይ የዕውቀትና የክህሎት ሥልጠና እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባ የአርባምንጭ መካነ ኢየሱስ ቴክኖሎጂና ቢዝነስ ኮሌጅ ገለጸ፡፡

በሶላር ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያገኙት ዕውቀትና ክህሎት ሥራ ፈጥረው ገቢ ከማግኘት ባሻገር ህብረተሰባቸውን ማገልገል እንደሚያስችላቸው አሰልጣኞች ተናግረዋል።

የአርባ ምንጭ መካነ ኢየሱስ ቴክኖሎጂና ቢዝነስ ኮሌጅ ከ50 ዓመታት በላይ በዕውቀትና በክህሎት የዳበሩ ዜጎችን ማፍራት የቻለ ኮሌጅ መሆኑ ተጠቁሟል።

ወጣቶች ሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸው በራሳቸው ገቢ መንቀሳቀስ እንዲችሉ የኮሌጁ የልማት ኮሚሽን ከጀርመን አድቬንቲስት ጋር በቅንጅት በመሥራት ወጣቶች በሶላር ቴክኖሎጂ በቂ ዕውቀትና ክህሎት ኖሯቸው በዘርፉ መሰማራት እንዲችሉ እየሰራ እንደሚገኝ የኮሌጁ ሁለንተናዊ የትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ፕሪንሲፓል አቶ ወንድሙ ወይኬ ተናግረዋል።

እንደ ወንድሙ ወይኬ ገለፃ በአሁኑ ጊዜ ሀገርቱ ያለችበት የኃይል ፍላጎትን ለማሟላት፣ በዘርፋ የሚሰማሩ ሥራ አጥ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግና የካርቦን ልቀት በአከባቢ ላይ እያስከተለ ያለውን ችግር ለመቅረፍ የሶላር ቴክኖሎጂ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ዘርፉ በስፋት እንዳልተሰራበት በመገንዘብ በቀጣይ በኮሌጁ እንደ አንድ የሥልጠና ዘርፍ እንዲከፈት የማድረግ ሥራ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

የግሪን ኢነርጂ TVET ፕሮጀክት ማናጀር አቶ አስመላሽ ዳኜ፥ በአርባ ምንጭ ከተማ 120 ወጣቶችን በሶላር ቴክኖሎጂ በማሰልጠን እውቀትና ክህሎት ኖሯቸው ሥራ ፈጥረው መንቀሳቀስ እንዲችሉ ስልጠናው ያግዛል ብለዋል።

Asmelash Dagne (Solar Technology Expert and Project Manager)

በሶላር ቴክኖሎጂ ዙሪያ ትምህርትና ስልጠና እየሰጡ ከሚገኙ መምህራን መካከል መምህር አዳሙ ሸዋ እና መምህር ጥላሁን አለምነህ ወጣቶች በዘርፉ በቂ ዕውቀትና ክህሎት እንዲኖራቸው ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ወጣቶቹ በሶላር ቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት ከማግኘትም ባሻገር ሥራ መፍጠር እንደሚችሉ እያስገነዘቡ መሆኑን ሌላኛው መምህር ወየሳ ወላንጎ ገልፀዋል።

Tilahun Alemnew (Solar Technology Instructor)

ከዩኒቨርሲቲ ተመርቃ የሥራ ዕድል ያላገኘችው ወጣት ቃልጊዳን ሕዝቅኤል በኮለጁ ለ3 ተከታታይ ወራት ስለ ሶላር ቴክኖሎጂና ሥራ ፈጠራ በቂ ዕውቀት እንደቀሰመች ተናግራለች።

ከሥልጠናው ወጣቶች በሶላር ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያገኙት ዕውቀትና ክህሎት ሥራ ፈጥረው ገቢ ከማግኘት ባሻገር ህብረተሰባቸውን ማገልገል እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል።

Kalkidan (One of the Trainees of Solar Technology)

ዘጋቢ፡ አማሮ አርሳባ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን ( South Radio and Television)

Avatar

By Guwad K.

Kaftle Torayto is a graduate of computer Science and Information Technology from Arbaminch Univeristy. His passion is writing, reading, listening music, graphics design and network engineering. Now days, he is working in Arbaminch Mekane Yesus Technical College.

Related Post